በዓለ ደብረ ቁስቋም
በዓለ ደብረ ቁስቋም ከሦስት የስደት እና መከራ ዓመታት በኋላ የአምላክ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልጇ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ይዛ አረጋዊ ዮሴፍንና ሰሎሜን አስከትላ ወደ ግብፅ ስትሰደድ በስተደቡብ የምትገኘው…
በዓለ ደብረ ቁስቋም ከሦስት የስደት እና መከራ ዓመታት በኋላ የአምላክ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልጇ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ይዛ አረጋዊ ዮሴፍንና ሰሎሜን አስከትላ ወደ ግብፅ ስትሰደድ በስተደቡብ የምትገኘው…
የጽጌ ጾም በዘመነ ሥጋዌ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሔም በተወለደ ጊዜ ንጉሥ ሄሮድስ ሥልጣኔን ይቀማኛል በሚል ቅናት ተነሣሥቶ ጌታችንን ለማስገደል አሰበ፡፡ ያንጊዜም ጌታችን በተአምራት መዳን ሲቻለው የትዕግሥት፣ የትሕትና አምላክ ነውና…
በወርኀ ጳጉሜን ከሚታሰቡ እና ከሚከበሩ በዓላት መካከል በየዓመቱ ጳጕሜን ፫ ቀን የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት በልዩ ልዩ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ይከበራል፡፡…
‹‹የሁለተኛው ወንዝ ስም ግዮን ነው:: እርሱም የኢትዮጵያን ምድር ሁሉ ይከብባል›› (ዘፍ. ፪:፲) ከኤዶም ፈልቀው ምድርን ከሚያጠጡት አራት ወንዞች ኤፌሶን፣ ጤግሮስ፣ ኤፍራጥስ፣ መካከል ሁለተኛው ግዮን ወይንም ዓባይ ወንዝ የሀገራችን ሲሳይ /በረከት/ እንደሆነ ቅዱሳት መጻሕፍት ምስክሮች ናቸው፡፡ ‹‹ወንዝም ገነትን ያጠጣ ዘንድ ከኤዶም ይወጣ ነበር፤…
በዓለ ጰራቅሊጦስ ዲያቆን ልሳነጽድቅ ኪዳነ መንፈስ ቅዱስ ከሚጠራባቸው ስሞች አንዱ ጰራቅሊጦስ ናዛዚ መጽንዒ መስተፍሥሒ፤ የሚያጽናና፣ የሚመክር፣ የሚረዳ፣ የሚታደግ የሚል ትርጉም አለው፡፡ አጽናኝም የተባለው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ‹‹አብ በስሜ የሚልከው…
“ዐርገ ሰማያተ በዐምደ ደመና፤ በደመና ወደሰማይ ዐረገ” (ቅዱስ ያሬድ) ዲያቆን ዐቢይ ሙሉቀን ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ይህን ቃል እንደተናገረው ዝማሬ በሚባለው የመጽሐፍ ክፍል እናገኘዋለን። ሊቁ የጌታችንን የማዳን ጉዞ ከፅንሰቱ ጀምሮ…
ሰሙነ ሕማማት በጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት እጅግ ከሚወደዱ እና ከሚናፈቁ ወቅቶች አንዱ ሰሙነ ሕማማት ነው፡፡ በዕለተ ሆሳዕና ጀምሮ በዕለተ ትንሣኤ የሚጠናቀቀው እጅግ ላቅ ያለ መንፈሳዊ ሕይወት የሚታይበት ጊዜ ነው፡፡ በላቲን Hebdomas Sancta or Hebdomas Maior፣ በግሪክ ደግሞ Ἁγία καὶ Μεγάλη Ἑβδομάς, Hagia kai Megale Hebdomas ታላቁ ሳምንት ተብሎ ይጠራል፡፡ በኛ ደግሞ ሰሙነ ሕማማት፡፡ የሕማማትን ወቅት ከመጀመርያው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ ክርስቲያኖች ያከብሩት እንደነበር የሚያሳዩ ጥንታውያን መዛግብት አሉ፡፡ በሕግ ደረጃ ክርስቲያኖች በሰሙነ ሕማማት ከማንኛውም ሥራ ነጻ ሆነው፣ ፍርድ ቤቶችም ተዘግተው እንዲከበሩ የወሰነው ደግሞ ታላቁ ቆስጠንጢኖስ ነው፡፡ እስከ አራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አዳዲስ ክርስቲያኖች ለመጠመቅ ይመርጡት የነበረው ጊዜ የትንሣኤን ቀን ነበር፡፡ ለዚህም ሁለት ዓይነት ምክንያቶች ነበሯቸው፡፡ የመጀመርያው ሰሙነ ሕማማትን በልዩ ሁኔታ ጾመው በትንሣኤው ቀን መጠመቁ ልዩ የሆነ መንፈሳዊ ኃይል ስለሚሰጥ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ እንደ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ትምህርት መጠመቅ ከክርስቶስ ጋር ሞቶ ከክርስቶስ ጋር መነሳት ነውና ጥምቀቱን ከትንሣኤው ጋር አያይዘውት ነበር፡፡ የሕማማት ሰሞን የኦሪት ጊዜን የሚያስታውስ ሰሞን ነው፡፡ አዳዲስ ክርስቲያኖቸም ይህንን ሰሞን ያለፈ ሕይወታቸውን ለማስታወስ እና ለማልቀስ ብሎም ራሳቸውን ወደ ሐዲስ ዘመን ለመለወጥ ይጠቀሙበት ነበር፡፡ በመጀመርያው መቶ ክፍለ ዘመን ከዓርብ ጀምሮ ሰሙነ ሕማማትን ማክበር የተዘወተረ ነበር፡፡ በሁለተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ግን ስድስቱንም ቀን ማክበር የክርስቲያኖች ሥርዓት እየሆነ መጣ፡፡ ለዚሀም መነሻ የሆነው የአባቶቻችን ቀኖና የተሰኘው ከሐዋርያት ዘመን ጀምሮ የተደነገጉ ቀኖናት መዝገብ በቦታው መዳረስ ነው፡፡ በዚህ መዝገብ ዐንቀጽ 5 ቁጥር 19 ላይ «በሰሞነ ሕማማት ከሳምንቱ ሁለተኛ ቀን (ሰኞ) እስከ ቅዳሜ የሰንበት መዘጋጃ ቀን ድረስ ጹሙ፡፡ በእነዚህም ጊዜያት ከእንጀራ እና ከጨው፣ ከማባያም በቀር ሌላ ነገር አትብሉ፡፡ ለመጠጥም ውኃ ብቻ ይሁንላችሁ» ይላል፡፡ የኛም ግብረ ሕማማት ይህንኑ የሐዋርያት ቀኖና በመጥቀስ በክፍል አንድ ሠላሳ አንደኛ ትእዛዝ በሚለው ርእስ ሥር «በሕማማት ሰሞን ከእንጀራ፣ ከጨው እና ከውኃ በቀር ምንም ምንም አትብሉ» ይላል፡፡ በ260 ዓም ለባሲሊደስ በጻፈው ደብዳቤ እያንዳንዷን የሰሞነ ሕማማት ቀን እና ሰዓት ከክርስቶስ መከራ ጋር በማያያዝ ገልጾ ነበር፡፡ በ2ኛው ወይንም በ3ኛው መክዘ ተሰባስቦ መጠረዙ የሚነገርለት የሶርያው ዲድስቅልያም ሰሙነ ሕማማት እንዴት መጾም እንዳለበት ይደነግጋል፡፡ አቡሊዲስ ዘሮም በጻፈው የሐዋርያት ትውፊት (215 ዓም) ስለ ሰሙነ ሕማማት ሥርዓት ይደነግጋል፡፡ እያንዳንዷንም ሰዓት ከክርስቶስ መከራ ጋር ያገናኛታል፡፡ ሰሙነ ሕማማት አሁን ያለውን መልክ የያዘው በ4ኛው መክዘ በኢየሩሳሌሙ ፓትርያርክ በቄርሎስ ዘመን ነው፡፡ ፓትርያርክ ቄርሎስ በመጨረሻዎቹ ዓመታት በኢየሩሳሌም ከሚከበረው የጌታችን ትንሣኤ በፊት ያለውን ሰሙነ ሕማማት እያንዳንዱን ቀን በማሰብ የሚከበርበትን ሥርዓት ሠርቶ ነበር፡፡ ከ381 እስከ 385 ወደ ኢየሩሳሌም ለመሳለም የሄደችው ኤገርያ የተባለች ስፔናዊ በኢየሩሳሌም እንዴት ሰሙነ ሕማማት ይከበር እንደነበር የታሪክ መዝገብ ትታልናለች፡፡ ኤገርያ በጉዞ ማስታወሻዋ እንዲህ ትተርክልናለች «በዓሉ የሚጀምረው በዕለተ እሑድ ነው፡፡ በዚህ ዕለት ስለ ዓልዓዛር ትንሣኤ የሚገልጠው የወንጌል ክፍል ጠዋት ይነበባል፡፡ በሆሳዕና ዕለት ከሰዓት በኋላ ሁሉም ሰው ወደ ደብረ ዘይት ይወጣል፡፡ ከዚያም በጸጥታ የዘንባባ ዛፍ ተሸክሞ ወደ ኢየሩሳሌም ይመለሳል፡፡ ይህንንም በመጀመርያዎቹ ሦስት ቀናት ይፈጽማሉ፡፡ ይህም ጌታችን ማታ ማታ ከከተማዋ ወጥቶ በደብረ ዘይት ያደረገውን ጸሎት ለማስታወስ ነው፡፡ በጸሎተ ኀሙስ ጠዋት ቅዳሴ ይቀደሳል፡፡ (ይህም በዓመቱ ውስጥ በመስቀሉ መቅደስ ላይ የሚደረግ ቅዳሴ ነው)፡፡ ከሰዓት በኋላ ሌላ ቅዳሴ ተቀድሶ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ቆስጠንጢኖስ ባሠራው በኤሊዎና ቤተ ክርስቲያን ሁሉም አብያተ ክርስቲያናት መብራት ያበራሉ፡፡ ከእኩለ ሌሊት በኋላ ደግሞ ወደ ጌቴ ሴማኒ ይጓዛሉ፡፡ በዚያም እስከ ንጋት ቆይተው የዓርብ ማለዳውን ወንጌል ለማንበብ ወደ ጎልጎታ ይመለሳሉ፡፡ ዓርብ ማለዳ ሁሉም መስቀሉን (በኢየሩሳሌም የነበረውን የጌታን መስቀል ነው) ቤተ ክርስቲያን አልባሳት ያስጌጡታል፡፡ ከስድስት እስከ ዘጠኝ ሰዓት ጌታችን በጎልጎታ በተሰቀለበት ላይ ሁሉም ተሰብስቦ ጸሎት ያደርሳል፣ ያለቅሳል፣ ያዝናል፡፡ በሠርክ ሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ወደ ስቅለቱ ቦታ በመጓዝ በዚያ ስለ ስቅለቱ እና መቃብሩ የሚገልጠው ወንጌል ይነበባል፡፡ ቅዳሜ ዕለት በየቤተ ክርስቲያኑ መብራት ይበራል፡፡» ሰሙነ ሕማማትን ልዩ በሆነ ሁኔታ የማክበሩ ሥርዓት ከኢየሩሳሌም በተሳላሚዎች አማካይነት ወደ ልዩ ልዩ ሀገሮች መግባቱ ይታመናል፡፡ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አበው ከኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ዘመን አንሥቶ ወደ ኢየሩሳሌም የመጓዝ ሥርዓት ነበራቸውና ይህንን ሥርዓት ቀድመው ሳይወስዱት አይቀሩም፡፡ ቅዱስ ያሬድ ለዚህ ሰሙን የሚሆን ሥርዓት መሥራቱን ስናይም ይበልጥ ያጠናክርልናል፡፡ ለመጀመርያ ጊዜ አሁን በምናየው መልኩ የሰሙነ ሕማማት ምንባባትን ያዘጋጁት የገዳመ መቃርስ መነኮሳት መሆናቸውን ግብረ ሕማማት ይገልጥልናል፡፡ በእነዚህ የገዳመ መቃርስ አባቶች በመታገዝ የእስክንድርያው ፓትርያርክ አቡነ ገብርኤል 2ኛ (1131-1145) (የኛ ግብረ ሕማማት "ጸሐፊ የነበረው የታሪክ ልጅ አባታችን አባ ቅብርያል" ይለዋል፡፡ ኢብን ቱርያክ የሚለውን ተርጉሞ ሳይሆን አይቀርም፡፡) በእርሱ አስተባባሪነት ሊቃውንቱ ለየቀኑ እና ለየሰዓቱ የሚሆኑትን ምንባባት ከብሉይ እና ከሐዲስ እያውጣጡ አዘጋጇቸው፡፡ ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ ደግሞ የብሕንሳው ጳጳስ አቡነ ቡትሮስ ምንባባቱን ለየሰዓታቱ በተመጣጣኝ ሁኔታ በማካፈል ሁሉም ቀናት ተመጣኝ የሆኑ ሁሉም ዓይነት ምንባባት እንዲኖሯቸው አድርገዋል፡፡ ግብረ ሕማማታችንም «ከኦሪት እና ከነቢያት፣ ከነዌ ልጅ ከኢያሱ፣ ከንጉሥ ሰሎሞን መጽሐፍ ወስዶ ሁላቸው ትክክል እስከሆኑ ድረስ በየሰዓቱ ሁሉ የሚገባውን አደረገ፡፡ አባቶች ከተናገሩት ሁለት ሁለት ተግሣፅ እና ምክር አንዱ በነግህ አንዱም በማታ እንዲነበብ አደረገ» ይላል፡፡ ግብረ ሕማማት ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ የተተረጎመበትን ራሱ ግብረ ሕማማት ይነግረናል፡፡ በመጽሐፉ መጨረሻ በሰላማ መተርጉም ጊዜ (1340 ( 1380) ገብቶ መተርጎሙን ያሳያል፡፡ በግብረ ሕማማቱ ያለው ምንባብ አንዳንድ ጊዜ ከግብፁ ግብረ ሕማማት ይበልጣል፡፡ በግብፁ ግብረ ሕማማት የሌሉት ተአምረ ማርያም እና ተአምረ ኢየሱስም ተካተተዋል፡፡ ይህም የኢትዮጵያ ሊቃውንት እጅ በትርጉሙ እና በዝግጅቱ ሥራ ላይ መኖሩን ያመለክተናል፡፡…