መድኅን፡ተወለደ

‘‘ሕፃን፡ተወልዶልናልና፡ወንድ፡ልጅም፡ተሰጥቶናልና፡
አለቅነትም፡በጫንቃው፡ላይ፡ይሆናል፡ስሙም፡ድንቅ፡
መካር፤ኃያል፡አምላክ፤የዘላለም፡አባት፤የሰላም፡አለቃ፡
ተብሎ፡ይጠራል’’።
ኢሳ፡ምዕ፡9፤6-7

መድኅን፡ተወለደ

የመድኃኒዓለም፡ክብር፡ለዓለም፡ተገለጠ፤
ለሰዎች፡መዳኛ፡ከአብ፡ዘንድ፡ተሰጠ፤
በቤተልሄም፡ተወልዶ፡ታሪክን፡ለወጠ።
በነብያት፡አባቶች፡በትንቢት፡ተነግሮ፤
ይኸው፡መጣ፡ዛሬ፡አክብሮ፡ቀጠሮ፤
በአማላጃችን፡በድንግል፡ላይ፡አድሮ።
የኢየሱስ፡መወለድ፡አስደንቆአቸው፤
ሰብአ፡ሰገል፡መጡ፡ወርቅ፡ዕጣን፡ይዘው፤
ኮከቡ፡መርቶአቸው፡መንፈስ፡ቀረቦአቸው፤
የአማኑኤል፡ፍቅር፡ከሩቅ፡ስቦአቸው።
የኢየሱስን፡ክብር፡ከዋክብት፡አሳዩ፤
እረኞችም፡አይተው፡ለሕፃኑ፡ዘመሩ፤
በዕውነት፡ተወለደ፡እያሉ፡አከበሩ።
መላዕክት፡በሰማይ፡የሚያመሰግኑት፤
ቅዱስ፡ነህ፡እያሉ፡ሰሙን የሚጠሩት፤
ሰዎችም፡አግኝተው፡በምድር፡ወደሱት፤
ክብር፡ልዕልና፡ኢየሱስ፡ነህ፡አሉት።
የአማኑኤልን፡ክብር፡እንስሳት፡አውቀው፤
በዛ፡በብርድ ወራት፡ተገኙ፡አብረው፤
ሙቀት፡እየሰጡ፡በትንፋሻቸው።
እሱ፡ሁሉ፡እያለው፡እንዳጣ፡ሰው፡ሆነ፤
ባንድ፡ጠባብ፡በረት፡እራሱን፡ወሰነ፤
ትህትናን፡ሊያስተምር፡የተከናወነ።
ሄሮድስ፡ሊያሰገድለው፡ሰዎችን፡ቢሰድም፤
ተልከው፡የሄዱት፡ቀሩ፡አልተመለሱም፤
በዕውነት፡የሱ፡ፍቅር፡ማንንም፡አይለቅም፤
ምንጊዜም፡አዲስ፡ነው፡ከቶ፡አይለወጥም።
የአዳምና፡የሔዋንን፡መርገም፡ለማጥፋት፤
ቤዛ፡ሆኖ፡ለማውጣት፡ከዲያብሎስ፡ግዛት፤
ይኸው፡ተወለደ፡የዓለም፡መድኃኒት፤
ሰውና፡መላዕክት፡ባንድ፡ላይ፡አዩት።
ዓለም፡ስትጨነቅ፡ኃጢአት፡ሞልቶባት፤
አንሰራፍቶ፡ይዞ፡ዲያብሎስ፡ሲመራት፤
መድኅኑ፡ክርስቶስ፡ተወለደላት፤
ለያዛት፡በሽታ፡ፈውስ፡ሊሆናት።

ኃይለመስቀል፡ተሰፋዬ

Close Menu